3 yrs ·Translate

________ • ምርጥ ጥንታዊ ባህላዊ ፍርድ

'ፕሮፌሰር ባህሩ ዘዉዴ' በፃፈዉ የ'ፊታዉራሪ ሀብተ-ጊዮርጊስ ዲነግዴ' ገድል ላይ አንድ የሚያዝናናኝ አጭር ታሪክ አለ።
ነገሩ እንዲህ ነዉ....

አንድ ሰዉ በምሽት ወደ ከተማ ወጣ ብሎ ሲናፈስ በጨለማዉ ግርግም ዉስጥ የቆመች ቆንጆ ሴት ያያል።
ጠጋ ብሎ ሲያናግራት የምሽት ሰራተኛ ሆና ኖሯል። 2 (ሁለት) ማርትሬዛ ሊከፍላት ተስማማ እና ቤቱ ይዟት ሄደ። ሌሊቱን በሙሉ ወዝ ሲቀያየሩ በተድላ አሳለፉ። ሰዉየዉም የምሽት ሰራተኛዋ ከጥቅምት ማር በላይ ስለጣፈጠችዉ ዛሬም እዚሁ ዉለሽ እደሪ አላት።

በዚህ ብቻ ሳይወሰን በየቀኑ እዚሁ ዉለሽ እደሪ እያላት እንደ ቀልድ 5 አመታቶች አለፉ። የሰዉየዉም ሀብት ተስፋፋ። በዚህ ጊዜ ቤተሰቦቹ አመፁበት። "ይቺን ሴተኛ አዳሪ አባር እና ጨዋ የጨዋ ልጅ አግባ!" እያሉ ወተወቱት። እሱም ምክራቸዉን ሰምቶ "ዉጭልኝ ከቤቴ!" አላት።

እሷም እያለቀሰች.. "ይሄን ሁሉ አመታት አንተ ጋር ኖሬ ምንም ንብረት ሳትሰጠኝ እንዴት እወጣለሁ?" እያለች አልቅሳ ብትለምነዉም እየገፈተረ ከቤቱ መነገላት።

የዚህን ጊዜ መኳንንቱ ጋር ሄዳ ከሰሰችዉ። ችሎት ተሰየመ። "የተጋባችሁበት ሰማኒያ አለ?" ብለዉ ጠየቋት መኳንንቱ። "የለም አልተጋባንም" አለች አቀርቅራ እያለቀሰች። "እና ሳትጋቡ እንዴት ሚስቴ ናት ብሎ ሀብት ያካፍልሽ? ዞር በይ ጥፊ!" ብለዉ አከላፍተዉ አባረሯት።

የዚህን ጊዜ የምሽት ሰራተኛዋ አንድ ነገር አስታወሰች። በፍርዳቸዉ ብልሃት የተነሳ አጤ ምኒልክ ' አባ-መላ' ብለዉ የሚጠሯቸዉ 'ፊታዉራሪ ሃብተ-ጊዮርጊስ ዲነግዴ' ትዝ አሏት። ቤታቸዉን አንኳኩታ 'አቤት!' አለች። ከእንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ሰዉየዉ ቀርቦ ችሎት ተሰየመ። አባ መላም እንደ መኳንንቱ ሁሉ ጠየቋት "ተጋብታችኋል?"

"አልተጋባንም" መለሰች።

"አይ የሴት ነገር 5 አመት ስትቀመጪ ያለምንም ሰማኒያ ነበር? ይሄማ ምኑን ንብረቱ ተገባሽ በይ! በፍፁም ሊያካፍልሽ አይገባም!" ሲሉ 5 ዓመታት ይዘዋት የተኙ ሰውዬ በደስታ መሬቱን መሳም ጀመረ። አባ መላም ወዲያዉ ቀጠል አድርገዉ ግን እንዲህ አሉ..

"ባይሆን ግን ያን ምሽት የተስማማችሁት በ 2 ማርትሬዛ አይደለም ? የእሱን የእያንዳንዱን ቀን 2 ማርትሬዛ አስልተህ የ5 አመቱን ስጣት!" አሉት ።

የ5 አመቱ 2 ማርትሬዛ ሲሰላ ከሰዉየዉ ጠቅላላ ሃብት በለጠ ::

ከ FB 😂