3 yrs ·Translate

#ታታሪ/ባለውለታ
Comedian Eshetu
➔መቼም እሼን የማያውቀው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ አለ ብዬ አላምንም። ትንሽ ነገር ስለሱ

➔እሼ በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ በተስፋፋበት ጊዜ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ማህበራዊ ሚዲያን ለዛ ባለውና ቀስ እያለ በሚወደድ መልኩ እየተጠቀመው ይገኛል።
➔በተለይ ድንቅ ልጆች በሚለው ፕሮግራሙ እጅግ ተወዳጅነትን ያተረፈ መሆኑ ይታወቃል። በተጨማሪም ለተለያዩ ተቋማት በቀጥታ ስርጭት በታቀደ ዓላማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ያካሂዳል፤ ዓላማውንም ያሳካል።
➔እሼ የዓላማ ሰው መሆኑን ያሳየ፣ ምንም ሳይበግረው በራሱ ጥረት አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰ ጠንካራ ሰው ነው።
➔እሸቱ ለኛ ተምሳሌት መሆን የሚችል ከትንሽ ተነስቶ (በተለይ በዩ ቲዩብ) ከ1 ሚሊዮን በላይ ተከታታይ (subscribers) ያፈራ (ይህም ማለት መልካም ነገሮችን በመከወን) ጎበዝ ወጣት በመሆኑ ለኛም ኩራታችን ሆኗል።
የዶንኪ ቲዩብ ሊንክ:- https://youtube.com/c/DonkeytubeEshetu2019

እሼ ካንተ ብዙ እንማራለን እናመሰግናለን🙏

image