friendtok friendtok
    #wisdom #market #disabilitysupport #kundli #best
    Advanced Search
  • Login
  • Register

  • Night mode
  • © 2025 friendtok
    About • Contact Us • Privacy Policy • Terms of Use • masterpage

    Select Language

  • English
  • አማርኛ
  • Oromifa
  • ትግርኛ

Events

Browse Events My events

Blog

Browse articles

Market

Latest Products

Pages

My Pages Liked Pages

More

Forum Explore Popular Posts Games Movies Jobs Offers Fundings
Events Market Blog My Pages See all
Dawit Gebreegziabher Tassew
User Image
Drag to reposition cover
Dawit Gebreegziabher Tassew

Dawit Gebreegziabher Tassew

@davo_68392
   
  • Timeline
  • Groups
  • Likes
  • Friends 539
  • Photos
  • Products
539 Friends
409 posts
Male
38 years old
Working at Addis Ababa Peace and security o
Studied at Addis Ababa uinversty MA project
Living in Ethiopia
Located in Addia Ababa Arada sub city Worda 4 house no 404 around international hotel
image
image
Dawit Gebreegziabher Tassew
Dawit Gebreegziabher Tassew
3 yrs ·Translate

#real is rear and #fake is everywhere
ረዘም ያለ ፁሁፍ ቢሆንም ሳትሰለቹ አንብቡት ‼️
✅የአንድ ተመራማሪ የዩኒቨረሲቲ መምህር (ፕሮፌሰር) በዚች ምድር ላይ 100% ለውጥ ማምጣት የሚችል ነገር ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ በተለምዶ የተለያዩ መልሶች አሉና እሱ ሳይንሳዊ እና ማትማቲካል በሆነ መንገድ መለየት እና ማረጋገጥ ፈለገ። ጥናቱንም መስራት ጀመረ‼️
👉በመጀመሪያ የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ ። A B C D E F G H I J K L M N O P Q R S T U V W X Y Z ። የእነዚህን ፊደላት ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ቁጥር ሰጣቸው። 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26
በጥናቱም ለእያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ ማለትም ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን ሰጠ። በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ። በተለይ እነዛን ለውጥ ለማምጣት ይረዳሉ እየተባሉ በየቦታው የሚነሱ ቃላትን ወሰደ እነሱም #hardwork #knowledge #love #luck #mony #leadership #attitude

1. #ተግቶ_መስራት
(H+a+r+d+w+o+r+k)
(8+1+18+4++23+15++18+11)=98%
2. #እውቀት
(K+n+o+w+l+e+d+g+e)
(11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96%
3. #ፍቅር
(L+o+v+e)
(12+15+22+5)=54%
4. #እድል
(L+u+c+k) = 47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም መቶ ፐርሰንት (100%) ለውጥ ሊሰጡ እንደማይችሉ አስቀመጠ ። ታዲያ (100%) ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው ? ገንዘብ ይሆን እንዴ ?
5. #ገንዘብ
(M+o+n+e+y)=(13+15+14+5+25)=72%
አይደለም ምን አልባት አመራር ይሆን ?
6. #አመራር
(L+e+a+d+e+r+s+h+i+p)
(12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97% አሁንም አይደለም! ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው ። አስተሳሰብ ፣ አካሄድ አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል ። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ
7. #አስተሳሰብ (አመለካከት)
(A+t+t+i+t+u+d+e)
(1+20+20+9+20+21+4+5)=100%
✅ የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው #የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ።
እና ምን ለማለት ነው የለውጥ መሰረቱ የአመለካከት መስተካከል ነውና መልካም እና ጠንካራ እሳቤ(አመለካከት ) ሊኖረን ይገባል፤ ለወደፊት የሚፈጠሩ ትውልዶችም ለሀገር ሸክም ሳይሆኑ ሀገርን ቢያንስ አንድ እርከን ከፍ እንዲያደርጉ አለመካከታቸውን ማረቁ ላይ በደንብ ልንሰራ ይገባል እላለሁ። ለዚህ ትልቁ ባለ ድርሻ በሁሉም ደረጃ ያሉ መምህራኖች ናውና ክብር ለመምህራኖቻችን‼️
✅👉 #real is rear and #fake is everywhere

Like
Comment
Share
avatar

Ake Akuni

Yes!!!
Like
· Reply · 1674372505

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

Dawit Gebreegziabher Tassew
Dawit Gebreegziabher Tassew
3 yrs ·Translate

#ስለ_ስጦታ_ሕግ_በጠቅላላዉ 🇪🇹

ስጦታ በአገራችን የፍትሐብሔር ሕግ ከተደነገጉት የውል ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ነው። በመሠረታዊው የውል ጽንሰ ሀሳብ ውል አንዱ ለሌላው የተወሰነ ነገር ሰጥቶ ወይም ፈጽሞ እርሱም በበኩሉ እንዲሁ የተወሰነ ነገር የሚቀበልበት ግንኙነት ነው።
በቀላል ምሳሌ በመኪና ሽያጭ ውል ውስጥ ሻጭ መኪናውንና ሥመ-ሀብቱን ለገዥ የማስተላለፍ ግዴታ አለበት። በአንጻሩ ገዥው የመኪናውን የሽያጭ ዋጋ ለሻጭ የማስረከብ ግዴታ አለበት። ይህም የተዋዋይ ወገኖችን ተነጻጻሪ መብትና ግዴታ (Reciprocity) ያሳያል። የዚህ ዓይነት በተዋዋይ ወገኖች ላይ ተነጻጻሪ ግዴታ የሚጥሉ ውሎች በዋጋ ላይ የተመሰረቱ ውሎች (Contracts on Onerous Title) ይሰኛሉ በሕግ አነጋገር።

ከዚህ የውል መሠረታዊ ጽንሰ ሀሳብ በተቃራኒው ግን የስጦታ ውል ተነጻጻሪ ግዴታ የሌለበት ውል ነው። በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2427 ላይ በግልጽ ሰፍሮ እንደምናነበው ስጦታ ማለት ሰጪ የተባለው አንደኛው ተዋዋይ ወገን ተቀባይ ተብሎ ለሚጠራው ለሌላ ሰው ችሮታ በማድረግ ሃሳብ ከንብረቶቹ አንዱን የሚለቅበት (ግዴታ የሚገባበት) ውል ነው።
ከዚህ የምንረዳው ስጦታ በመርህ ደረጃ ግዴታን በአንዱ ወገን ትከሻ ላይ የሚጥል፤ መብትን ደግሞ ለሌላኛው ወገን እንደሚያጎናጽፍ ነው። በሌላ አነጋገር በስጦታ ውል ውስጥ ስጦታ ሰጪው የመስጠት ግዴታ (Unilateral Obligation) ያለበት ሲሆን፤ ስጦታ ተቀባዩ ግን ከመቀበል መብት በስተቀር ተነጻጻሪ ግዴታ የለበትም።
እናም ስጦታን ጨምሮ በአንድ ወገን ላይ ግዴታ የሚጥሉ ውሎች በችሮታ ላይ የተመሰረቱ (Contracts on Gratuitous Title) ይባላሉ። ያለክፍያ የሚደረጉ የአደራ ውሎችና የውክልና ውሎችም ልክ እንደስጦታ ውል ሁሉ በችሮታ ላይ የተመሰረቱ ውሎች ምድብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

እዚህ ላይ አንድ ወገን ብቻውን ተጠቅሞ ሌላው ወገን ለምን ተገዳጅ ይሆናል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። «የውል ግንኙነት የግለሰቦችን የፍትሐብሔር መብትና ግዴታ የሚመለከት በመሆኑ ወዶና ፈቅዶ በሕግ አግባብ እስካደረገው ድረስ አንድ ሰው በፍትሐብሔር መብቱ ላይ በመሰለው ሊያዝበት ይችላል» ይላሉ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ «የኢትዮጵያ የውል ሕግ መሰረተ ሀሳቦች» በሚለው መጽሐፋቸው ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ከሚዋዋለው ሰው ጋር ያለውን ቤተሰባዊ ግንኙነት፣ ቀደም ሲል ያደረገለትን ውለታ ወይም በጎ ሥራ፤ ወይም ሃይማኖታዊና ሰብዓዊ እሴቶቹ አስገድደውት ስጦታ ቢያደርግ የመብቱ ባለቤት እራሱ ስለሆነ ለምን ይህንን አደረክ ሊባል አይገባውም።

#የስጦታ_ልዩ_ባህርያት 💥

በመርህ ደረጃ ስጦታ የሰጪ የራሱ የተለየ ተግባር ወይም ጥብቅ የሆነና ራሱ የሚፈጽመው ሕጋዊ ድርጊት ነው። ያም ሆኖ የሚሰጡት ንብረቶች እንዴት ያሉ እንደሆኑና ለማን እንደሚሰጡ በግልጽ በማስታወቅ ስጦታ በተወካይ አማካኝነትም ሊፈጸም ይችላል።

የስጦታ ውል ፍጹም እንዲሆን የተቀባዩም ፈቃድ ያስፈልጋል፤ ማለትም «ልግስናውን እቀበላለሁ» ብሎ ሃሳቡን መግለጽ አለበት። ስጦታውን የስጦታ ተቀባዩ እንደራሴ ስለእርሱ ሆኖ ሊቀበልለት ይችላል። የተቀባዩ ወራሾች ግን ስለእርሱ ሆነው ስጦታን መቀበል አይችሉም።

ከዚህ የምንረዳው ታዲያ ስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን የግራቀኙ ሀሳብ ለሀሳብ መገናኘት የግድ አስፈላጊ መሆኑን ነው። ስጦታ ሰጪው (ውል ሰጪው) ውል የማድረግ ፍላጎቱን (የችሮታ ሀሳቡን) ለስጦታ ተቀባዩ (ለውል ተቀባዩ) በማያሻማ መልኩ መግለጽ አለበት። የውል አቀራረብ (Offer) መኖር አለበት ማለት ነው። ይህንንም ስጦታ ተቀባዩ በሙሉ ልቡና ሃሳቡ ከተቀበለው የውል አቀባበል (Acceptance) በመኖሩ በመካከላቸው ያለው የመዋዋል ፍላጎት ተቋጨ ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ልግስናውን እንካ ተቀበል እየተባለ እቀበላለሁ ብሎ ሀሳቡን ሳይገልጽ ከቆየ ወይም ዝም ብሎ ከርሞ ሰጪው ከሞተ ወይም ችሎታ ካጣ (በሕግ ወይም በፍርድ ክልከላ ከተጣለበት አልያም አዕምሮው ከጎደለ) በኋላ ስጦታውን እቀበላለሁ ቢል በሕግ ፊት ዋጋ የለውም።

ልብ ሊባልበት የሚገባው ሌላው ጉዳይ በኑዛዜ የሚደረግ ስጦታ በሕግ እይታ ውል ሊባል እንደማይቻል ነው። እርግጥ ነው በኑዛዜ ውስጥ ሟቹ ንብረቶቹን ለኑዛዜ ስጦታ ተቀባዮች ሊሰጥ ይችላል። ነገር ግን የተቀባዩ ፈቃደኛ አለመሆን ኑዛዜውን ፈራሽ አያደርገውም። ተቀባዩ የኑዛዜውን ስጦታ አልቀበልም ካለ በሕጉ መሠረት ንብረቱ ከሟች በአደራ ለተቀበለው ሰው ይተላለፍለታል። ከዚህ ሌላ የስጦታ ውል የሚፈጸመው ወይም እንደውሉ ተቀባዩ ንብረቱን የሚወስደው ሁለቱም በሕይወት ሳሉ ሲሆን ኑዛዜ የሚፈጸመው ወይም የኑዛዜው ቃል ተግባራዊ የሚደረገው ደግሞ ተናዛዡ ከሞተ በኋላ ነው፡፡

ስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን የሚደረግበት ሥርዓትና ፎርም በሕጉ ተደንግጓል። በዚሁ መሠረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብትን የሚሰጥ ስጦታ (በንብረቱ መገልገል ወይም አላባውን/ፍሬውን መጠቀም) ሰጪው እየተናገረ ማናቸውም ሌላ ሰው በሚጽፍለት ወይም ራሱ ሰጪው በምስክሮች ፊት በሚጽፈው ሰነድ ላይ እንዲሰፍር ካልተደረገ ፈራሽ ነው። በመዝጋቢ አካል እንዲመዘገብ ግን አይጠበቅም።

ተንቀሳቃሽ ንብረቶችንና ለአምጪው የሚከፈሉ ሰነዶችን (እንደ ቼክ ያሉ) የተመለከቱ ስጦታዎች ደግሞ እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ይፈጸማሉ። ያም ሆኖ ስጦታ ሰጪው የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ ለማድረግ በሚያደርገው ዓይነት ፎርም ጽፎ ስጦታውን እንዳያደርግ የሚከለክለው ሕግ የለም። ከዚህ ውጪ ስጦታ ሰጪው ሌሎች መብቶቹን ወይም ከሦስተኛ ወገኖች ጋራ የተዋዋለበትን ጥቅም የሚያስገኝ የውል ሥምምነትንም ለስጦታ ተቀባይ በመስጠት ብቻ የስጦታ ውል ማድረግ ይችላል።
ስጦታን በተመለከተ በሰጪውና በተቀባዩ እንዲሁም በሦስተኛ ወገኖች መካከል አለመግባባት ተነስቶ ወደ ክርክር ቢያመሩ የማስረጃ ጉዳይ መሠረታዊ ጥያቄ ነው። በሕጋችን ስጦታ ስለመኖሩ የማስረዳት ሸክሙ ስጦታ አለ በሚለው ተከራካሪ ወገን ትከሻ ላይ ነው የወደቀው። ስጦታ አለ የሚለው ሰው ስጦታ መኖሩን ማስረዳት አለበት፡፡

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና በጠቃ
0911 190299

⭕️ #ተጨማሪ መረጃዎችን ሊንኩን 👇 ተጭነዉ በነጻ ያግኙ 👇

👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw

#ethiopia #legalservice #lawyer #samuelgirma #tebeka #addisababa 🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹

Like
Comment
Share
avatar

Endris Muktar

Best
Like
· Reply · 1673884959

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

Dawit Gebreegziabher Tassew
Dawit Gebreegziabher Tassew
3 yrs ·Translate

የውል አጻጻፍ ስርዓት/የውል አመሠራረት መርሆዎች/
=====================
በኢትዮጵያ የውል ሕግ የውል አመሰራረት መሠረታዊ መርህ በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በስተቀር ለውል መመስረት በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው፡፡
የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1719/1/ በጠቅላላው ሥርዓት በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ ስምምነት ውል ለማድረግ በቂ ነው በማለት ይደነግጋል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በሁለት ተዋዋዮች መካከል በህግ የሚፀና ሕጋዊ ውጤት ያለው ውል ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ነው፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ የውል ሕግ የውል አመሰራረት መሠረታዊ መርህ በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በስተቀር ለውል መመስረት በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው የሚለው ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ውል ህጉ ያስቀመጠውን የፎርም መስፈርት አያሟላም ተብሎ ውድቅ ሊደረግ የሚችለው ይህን ውል የሚመለከት በግልጽ የተቀመጠና የተለየ የአጻጻፍ ሥርዓት /ፎርም/ መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ህጉ የተለየ ጽሁፍ የሚጠይቅ በሆነ ጊዜ ይኸው ሥርዓት እስካልተሟላ ድረስ ውሉ አንደረቂቅ ከሚቆጠር በቀር በተዋዋዮች መካከል የሚፀናና አስገዳጅነት ያለው ህጋዊ ግንኙነት ሊመሰረት አይችልም፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ውል በተለየ ፎርም እንዲፈፀም ግድ የሚሆነው ውሉ፤ 1. ባለቤትነትን /ownership/ 2. የአላባ ጥቅምን /usufruct/ 3. መያዣን /mortgage/ ወይም 4. ሌላ አገልግሎትን (servitude) ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የተደረገ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
አንድ ውል የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከትም ቢሆን ከእነዚህ ውሎች በአንዱ ውስጥ የሚካተት እስካልሆነ ድረስ በተለየ ፎርም መከናወን የለበትም፡፡ ከእነዚህ ውሎች በአንዱም ውስጥ ከማይካተቱና በዚህም ምክንያት የተለየ ፎርም ከማያስፈልጋቸው ውሎች መካከል የኪራይ ውል አንዱ ነው፡፡ በሌላ በኩል ሕጉ ከሚያስቀመጠው አስገዳጅ ፎርም ውጪ ተዋዋይ ወገኖች የውላቸው አፈፃፀም ልዩ በሆነ አጻጻፍ ሥርዓት ሊወስኑት እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1719/3/ ይደነግጋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ተዋዋዮቹ ሕጉ የማያስገድደውን ፎርም ለመፈፀም የተስማሙ እንደሆነ ውሉ ፍጹም የሚሆነው የተስማሙበትን የውላቸውን አፈጻጸም ሞልተው ሲዋዋሉ ብቻ እንደሆነ የሕጉ ቁጥር 1721 ይደነግጋል፡፡ በዚህ ህግ መሠረት የፎርሙን ዓይነትና ይዘት የሚወስኑት ተዋዋዮቹ ራሳቸው በመሆናቸው ሊከተሉ ስለፈለጉት ፎርም በመካከላቸው ግልጽ የሆነ ስምምነት መኖር ይገባዋል፡፡፡ በቁጥር 1719 እንደተገለፀው በመርህ ደረጃ ውል ለመዋዋል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ በመሆኑ ውሉ እንዲፀና ተዋዋዮቹ እንዲፈፀም የፈለጉት ተጨማሪ ፎርማሊቲ ምን እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ተዋዋዮቹ ባደረጉት ውል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የፎርሙን አይነት የምስክሮቹን ብዛት፣ ስለመመዝገብ አስፈላጊነት፣ አዋዋይ ፊት ስለመቅረብ ወ.ዘ.ተ ተዋዋዮቹ በፍላጎት የጨመሩት ፎርም ስለመኖሩ በተዋዋዮቹ መካከል ከተደረገው ስምምነት መገንዘብ መቻል አለበት፡፡
ተዋዋዮቹ ውላቸውን በጽሁፍ ካሰፈሩ የጽሁፍ ፎርማሊቲ እንደፈለጉ መገመት ቢቻልም ይህ በጽሁፍ የሰፈረው ስምምነት በምስክሮች እንዲረጋገጥ ወይም እንዲመዘገብ፣ ወይም አዋዋይ ፊት እንዲቀርብ መፈለጋቸውን የሚያሳይ አይሆንም፡፡ በጽሁፍ ከመሆኑ በተጨማሪ ሌሎቹም ፎርማሊቲዎች እንዲሟሉ መፈለጋቸው በጽሁፉ በራሱ ወይም በሌላ መልክ ስምምነት መኖሩን የሚያሳይ ነገር መኖር አለበት፡፡
ሰ/መ/ቁ. 15992 ቅጽ 1፣ ፍ/ህ/ቁ. 1719-1721
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በፅሁፍና ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፊት ወይም በፍ/ቤት ካልተደረገ ውጤት የሌለው መሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 ስር ተመልክቷል፡፡ ይህን በሕጉ የተመለከተው የአፃፃፍ ስርአትን አለመከተል የሚያስከተለው ውጤት ምን እንደሆነ ደግሞ በዚሁ ሕግ ቁጥር 1808/2/ ስር ተቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት የአፃፃፍ ስርአት ያላሟላ ውል የሚፈርሰው ከተዋዋዮቹ በአንዱ ወይም ማናቸውም ጥቅም ያለው ሰው ሲጠይቅ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ይህም አንድ የአፃፃፍ ስርአትን ያላሟላ ውል በሕጉ በተመለከቱት ሰዎች እንዲፈርስ ጥያቄ አስካልቀረበበት ድረስ ከጅምሩ ፈራሽ ነው ሊባል እንደማይችል ያስገነዝበናል፡፡ ውሉ የአፃፃፍ ስርአትን ባለመከተሉ ምክንያት እንዲፈርስ ጥያቄ እስካልቀረበ ፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት የአፃፃፍ ስርዓቱን ምክንያት በማድረግ ውሉን ከጅምሩ ውድቅ ሊያደርግ የሚችልበት የሕግ ምክንያት የለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43825 ቅጽ 10፣ ፍ/ህ/ቁ. 1808(2)

Like
Comment
Share
avatar

Meti Arega

Tnx
Like
· Reply · 1673775715

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

avatar

Aser Berhanu

10q
Like
· Reply · 1673778525

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

avatar

Ake Akuni

OK
Like
· Reply · 1673790561

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

Dawit Gebreegziabher Tassew
Dawit Gebreegziabher Tassew
3 yrs ·Translate

ሰው በገዛ አዕምሮው ላይ ባለስልጣን ነው፡፡ የስልጣኑ ወሰንም አዕምሮውን፣ ስሜቱን፣ ፍላጎቱንና መንፈሱን እስከመምራት የሚያደርሰው ታላቅ ስልጣን ነው፡፡ ነገር ግን እሱ ይመራው ዘንድ የተፈጠረለትን አዕምሮ መምራት አቅቶት በሱ የሚመራ ከሆነ ግን የተሰጠውን ስልጣን አባክኗል፤ ወይም በስልጣኑ አልተጠቀመም ማለት ይቻላል፡፡

አንዳንድ ሰው የራሱን አዕምሮ #ዝግ ያደርገዋል፡፡ እንዲያውቅ፣ እንዲመራመር፣ እንዲሰለጥን፣ አዳዲስ መንገዶችን እንዲፈትሽ ዕድል አይሰጠውም፡፡ ቀድሞ ባወቀው ወይም የቅርብ ሰዎቹ ያሳዩትን መንገድ ብቻ የሙጥኝ ብሎ ከራሱ የሕይወት ጎዳና ጋር ይጠፋፋል፡፡ የራስን ዘንግቶ የሌላ ሰውን የሕይወት መንገድ የመፈለግ ያህል ኪሳራ የለም፡፡ የገንዘብ ኪሳራ በስራ ይመለሳል፤ የአዕምሮ ኪሳራ ግን ዕድሜን ሁሉ ያከስራል፡፡

አዕምሮ በራሱ አያድግም፤ አስተሳሰብ ከመሬት ተነስቶ አይበስልም፤ ዕውቀት ወፍ ዘራሽ አይደለም፤ መልካም ሃሳብ ተዘርቶ፣ አዕምሮው ታርሶ፣ የክፉ አስተሳሰብ አረሙ ተነቅሎ፤ ሃሳቡ ተኮትኩቶ የሚበቅል እንጂ፡፡

ባለአዕምሮው፣ ባለሃሳቡ አዕምሮውን ለማስተማርና ለማሰልጠን ካልፈቀደና በተግባር ሊሰራበት ካልቻለ የሩቁን ቀድሞ የማይመለከት፣ የማይታየውን የማያይ ድንክ አስተሳሰብ ይይዛል፤ ወንዝ የማያሻግር የጎጥ አመለካከት ባለቤት ይሆናል፡፡ ማንም #አዳጊ #አዕምሮ መፍጠር ካልቻለ ሕሊናው ተቸንክሮ እንዲቆም የበኩሉን ሚና ተወጥቷል ማለት ነው፡፡

ሰው አካላዊ ቁመቱን የማሳደግ ችሎታ ባይሰጠውም፤ የራስ ፀጉሩን አንዲት ዘለላ ለመጨመር ጥበብ ባይኖረውም #አዕምሮውን #የማሳደግ፣ ሕሊናውን የማጎልበት፣ ስሜቱን የማብሰል፣ መንፈሱን የማሰልጠን፣ የዕይታ ቁመቱን የማስረዘም ታላቅ አቅም አለው፡፡ የሰው ልጅ አዕምሮ በባለአዕምሮው ግለሰብ እንደሚቀረፅ እርሳስ ነው። ባለቤቱ ቀርፆ ሹል ካደረገው የሚሾል፤ ከተወውም ዶምዱሞ የሚቀር ነው፡፡

በጭብጨባ የማይጠፋ በትችትም አንገት የማይደፋ ህሊና ብስል ሕሊና ነው፡፡ በአድናቆት የማይኮፈስ፤ በውግዘትም የማይወድቅ ማንነት ሊሰራ የሚችለው አዕምሮን በመልካም ሃሳብና በመንፈሳዊ እውቀት መሙላት ሲቻል ነው፡፡ የጎደለ አዕምሮ ጎዶሎ ያደርጋል፤ ያነሰ ሃሳብ ያሳንሳል፡፡ በትናንሽ ፈተናዎች የማይደነግጥና ወድቆ የማይቀር ማንነት ራሱን ለምንም ያዘጋጀና በመከራ ተፈትኖ የሚያልፍ ነው፡፡ ሂስ ለመቀበል የፈቀደ አዕምሮውን ለማስተማር ቆርጦ የተነሳ ነው፡፡

አድናቆት ብቻ የሚፈልግ ሂስን እንደጦር የሚፈራ ማንነት ግን ራሱን ለማስተማር የማይሻ ነው፡፡ #የቆመ #አዕምሮ #አያድግም፣ #አይማርም፣ #አይሰለጥንም፡፡ አዕምሮውን ያቆመ ሰው ቀድሞ ያወቀውን ወይም የተነገረውን ብቻ ይዞ ሕይወትን በአንድ አቅጣጫ የሚመለከት፤ ዓለሙን በጠባብ አስተሳሰቡ የሚደመድም #የውስን #አዕምሮ ባለቤት ይሆናል፡፡

በዚህ ዘመን አውቀዋል የሚባሉ አብዛኛው ምሁራን በሞራል ልዕልና፣ በሰውነት ጥበብ፣ በመንፈሳዊ ስልጣኔ ወደኋላ ቀርተዋል፡፡ #የእንጀራ #ዕውቀት ብቻ ይዘው ዓለሙን በጭላንጭል እይታ የሚደመድሙ አዋቂ ተብዬዎች በርክተዋል፡፡ #አስተሳሰባቸውን #ገድበው ሌሎችን ለመረዳት የማይሹ፤ #የአዕምሮ #በራቸውን #ጥርቅም አድርገው #የዘጉ፣ በሃሳባቸው ላይ የተለያየ ሃሳብ የማይጨምሩ ቆሞ ቀሪዎች ናቸው ሐገራችንን ወደኋላ እንድትምዘገዘግ እያደረጉ ያሉት፡፡ ምርጫ መቀስቀስ እንጂ ለህዝብ መስራት የማይችሉ ድኩማን ናቸው ሐገሬን የሚያሸብሩት፡፡ ይህ ዘመን ቃላቸው ከልባቸው ያልተዛመደ፤ ፉከራቸው ከዕውቀታቸው ጋር ያልተዋሀደ የበዙበት ዘመን ነው፡፡ .....

ዘንድሮ አፉ ከልቡ የማይስማማ ሰው በዝቷል፡፡ ወሬው ሌላ፤ ተግባሩ ሌላ፡፡ ጉራው ሌላ፤ ዕውቀቱ ሌላ፡፡ ሃሳቡ የተበታተነ፤ አንድን ነገር በአትኩሮት ጀምሮ የሚጨርስ ጠፍቷል፡፡ ለወገኑ ጠብ የሚል ሳይንሳዊ መፍትሄ ሳይፈጥር ፈረንጅ የጋተውን መረጃ የሚያነበንብ የጥቁር-ነጭ በዝቷል፡፡ የተማረ ለመምሰል እንጂ ለመማር የፈቀደ የለም፡፡ #ያወቀውን #በቀናነት #አሳውቆ #ለወገኑ የሚደርስ ወገን ደራሽ አንሷል፡፡

ጀማሪ የበረከተባት ጨራሽ ያነሰባት ሐገር ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ከቃሉ ጋር የተፋታ፣ ሕሊናውን የከዳ፣ ለታይታ ብቻ የሚኖር ነው ሐገሬን ያጥለቀለቀው፡፡ አቋሙን ያጸና፤ ለህሊናው የሚሟገት፤ ለእውነት የሚቆም ሰው ማግኘት አዳጋች ሆኗል፡፡ ሃይማኖቱ የአፍ፣ ፀሎቱ የውሸት፣ ዕቅዱ ግብ የማይመታ፣ በአቋራጭ ለመክበር የሚቸኩል እንጂ በትዕግስትና በስራ፣ በእምነትና በእውነት ያሰበውን ለመፈፀም የታመነ መንምኗል፡፡

የዚህ ሁሉ ችግር መንስኤ #አብዛኛው #ሰው #ለአዕምሮው #የሚሰጠው #ቦታ #ለሆዱ #ከሚሰጠው #በጣም #ያነሰ #በመሆኑ ነው፡፡ ሰው ሁልጊዜ አዕምሮውን ለማሳደግ ቢፍጨረጨር አፉና ልቡ የተስማማ፤ ቃሉና ስራው የተዋሃደ፤ ለእውነት የሚቆም ለቃሉ የሚታመን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሕሊናውን መመገብ ያልቻለ የሃሳብ ጠኔ ይወርሰዋል፤ ጥበብ ይታረዛል፤ ዕውቀት ይራባል፡፡ አካሉ ቢንቀሳቀስም አዕምሮው እየተንቀሳቀሰ አይደለም፡፡ መራመድ ቢችልም በሃሳብ ወደፊት መጓዝ አይችልም፡፡ በአንድ ጥግ #እንዲቆም #የተደረገ #አዕምሮ አማራጭ መንገድ የለውም፡፡ በለመደው ጥግ እንደቆመ ጊዜ ያልፍበታል፤ እድሜውም ይባክናል፤ ሐገሩንም ወደኋ ያስቀራል፡፡

የተከፈተ ልብ! አዳጊ አዕምሮ!

ፀሐፊው:- እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

Like
Comment
Share
avatar

Getabalew Fenta

Absolutely
Like
· Reply · 1673764202

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

avatar

Meti Arega

Lk nw
Like
· Reply · 1673775798

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

avatar

Aser Berhanu

Dude
Like
· Reply · 1673778607

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

Dawit Gebreegziabher Tassew
Dawit Gebreegziabher Tassew
3 yrs ·Translate

ከድፍረት ሁሉ ምርጡ ድፍረት በአስተሳሰብህ ደፋር መሆን ነው!
(Dare to think the unthinkable!)
(እ.ብ.ይ.)

በሐገራችን ክፉ ሰው ሰውን ይደፍራል፡፡ ነገረኛ ሰው ሰውን በነገር ይተነኩሳል፡፡ ለካፊ ሰው ሰውን ይለካክፋል፡፡ ብቸኛውን የሚያሸማቅቅ ዘመደ ብዙ በየመንደሩ ሞልቷል፡፡ ሆነ ብሎ ነገር እየፈለገ የሌላ ሰውን ህይወት የሚረብሽ ብዙ ነው፡፡ ድፍረቱን የሚጠቀምበት ለእኩይ ነገር ነው፡፡ ወንድነቱን የሚያሳየው በጉልበቱ ነው፡፡ የሰውን መብት ለመቀማት፤ ነፃነቱን ለመግፈፍ ያሰፈሰፈ የሰፈርና የቀበሌ ጉልቤ መዓት ነው፡፡ በየመንግስት መስሪያቤቱ የድሃን መብትና ጥቅም የሚመነትፍ ህጋዊ ሌባ በሽ ነው፡፡ በመዋቅር ክለሳ ሰበብ የራሱን ሰው የሚሰገስግ፣ የወንዙን ሰው የሚሸጉጥ ዘረኛ ሁሉ በኮሚቴ ስም ስራውን ይሰራል፡፡ አብዛኛው ሹመኛ ስልጣኑን የሥራ ማስፈፀሚያ ሳይሆን የግል ፍላጎቱን መወጣጫ የሚያደርግ ነው፡፡ ፖለቲከኛው ፖለቲካውን ለሐገርና ለወገን ጥቅም ሲባል ማዘመን ሳይሆን ፖለቲካው ለእሱ እንዴት እንደሚጠቅመው አድርጎ ያጣምመዋል፡፡ ሐገራዊ ፕሮጀክቱን ለከርሱ ፍጆታ ያውለዋል፤ ህጉን ያስቀይሳል፤ ስትራቴጂውን አንጋዶ ይተገብራል፤ ፖሊሲውን አይረዳም፤ ህገመንግሰቱን አጣምሞ ይተረጉማል፤ ፍትህን ደሃ የማይደርስበት ሰማይ ላይ ይሰቅለዋል፡፡ አዕምሮው ለተንኮል እንጂ ለበጎ ምግባር አልተዘጋጀም፡፡ በኢትዮጵያችን በሃሳብ ወንድ የሆነ፤ በአመለካከቱ ደፋር የሆነ ማግኘት ብርቅ ነው፡፡ ለበጎ ነገር የቀደመ ግንባርቀደም ዜጋ ተቸግረናል፡፡

በአስተሳሰብ ደፋር መሆን ማለት ብዙ ሰው ለማሰብ የማይደፍረውን ማሰብ መቻል ማለት ነው፡፡ ብዙ ሰው የሚያስበው በተመሳሳይ መንገድ ነው፡፡ ሰው አስቦበት በማያውቅ መንገድ ማሰብ ያሥወግዛል ወይም ውጉዝ ከመአርዮስ ያስብላል፡፡ ሰው ያላየውን ማየት፣ ያልሰማውን መስማት፣ ያላነበበውን ማንበብ፣ ያልተረዳውን መረዳት፣ ያላሰበውን ማሰብ መቻል በጎ ድፍረት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ድፍረት ለአሳቢው ብቻ ሳይሆን ለሐገሩ የሚያዝና የሚጨበጥ አዲስ መላ ይፈጥራል፡፡ ብዙዎቹ ታዋቂ ሳይንቲስቶችና ፈላስፋዎች ሰው ባላሰበበት መንገድ አስበው ነው ዓለማችንን አሁን ለደረሰችበት ስልጣኔ ያደረሷት፡፡

በእኛ ሐገር ሰው በተለየ መንገድ ሲያስብ አይበረታታም፡፡ ጥንትም ሆነ ዛሬ አንድ ለሐገሩ ተቆርቋሪ የሆነ ዜጋ መንግስትን ለምን ብሎ ከጠየቀ ታርጋ ይለጠፍበትና እስርቤት ይታጎራል፡፡ ወዳጅ፣ ዘመዱን፣ ባልንጀራውን ስለእውነት ብሎ በአመክንዮ የሚሞግት ይጠላል፡፡ ሀገራችን አሳቢን አታበረታታም ማለት ይቻላል፡፡ ከራስህ ጋር ስትነጋገር፣ ሃሳብህን ስታሰላስል፤ ዓለሙን ስትመራመር፣ በተፈጥሮው ስትመሰጥ፣ ዩንቨርሱ ላይ ስትፈላሰፍ ያየህ የሀገርህ ሰው ስም ይሰጥሃል፡፡ ለፍልስፍና ያለው አመለካከት ልክ አይደለም፡፡ እሱ ላንተ ሃሳብ ግድ የለውም፡፡ ‹‹ሊያብድ ነው፤ ሊቀውስ ነው›› እያለ ከመንጋው ይነጥልሃል፡፡ በማሰብህ ትገለላለህ፡፡ ለምን፣ እንዴት ብለህ ስትጠይቅ በማህበረሰቡ የተረብ ዱላ ትወገራለህ፡፡ የተለየ በማሰብህ ትለያለህ፡፡ በአስተሳሰብህ መንደሩ ይቆነጥጥሃል፤ ለምን ስትል ሹመኛው ይኮረኩምሃል፣ ስለእውነት ስትሞግት ወዳጅ ዘመድህ ያሽሟጥጥሃል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያ በአገቱኒ መፅሐፋቸው ገጽ 81 ላይ ያቀረቡት ቀልድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል፡፡

‹‹በሎንደን ከተማ የመንግስታት ሰላዮች ስብሰባ ነበረ፡፡ የእንግሊዙ ተወካይ ወንጀለኛን ለመያዝ ብዙ ወራት አንዳንዴም ዓመታት እንደሚፈጅባቸውና ይሄን ረጅም ጊዜ ለማሳጠር ሙከራ ላይ መሆናቸውን ተናገረ፡፡ አሜሪካዊውም ተመሳሳይ ችግር አነሳ፡፡ ኢጣልያንና ስፔን ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚፈጅባቸው ጊዜ በሳምንት የሚቆጠር ጊዜ መሆኑን በኩራት ተናገሩ፡፡ የሩሲያና የቻይናም ተወካዮችም በቀናት የሚቆጠር ጊዜ ብቻ እንደሚያስፈልጋቸው ኮራ ብለው ገለፁ፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ መልዕክተኛ እየተኩራራ ‹‹በሌላ ሁሉ ቀድማችሁን ብትገኙም በዚህ ጉዳይ ግን ጥለናችሁ ሄደናል፡፡ እኛ ወንጀለኛውን የምንይዘው ገና ሲያስብ ነው›› .... በማለት የድፍረቱን ከፍታ አሳየ፡፡

ይሄ ቀልድ መራራ ሃቅ ነው፡፡ ልዩ ሃሳብ የሚያስብ ሰው ይሳደዳል፤ ይያዛል፡፡ የሚጠይቅ ሰው ይታሰራል፡፡ ለምን እንዴት የሚል ሰው ከወዳጅ ዘመድ ጉባኤው ይገለላል፡፡ በተለየ መንገድ የሚያስብ ሰው አይወደድም፡፡ ስለእውነት ብሎ የሚታገል በሀገራችን ቦታ የለውም፡፡ የደሃን ጩኸት የሚሰማ ጆሮ እምብዛም ነው፡፡ ሁሉም ምላስ ብቻ ሆኗል፡፡ ሁሉም ይናገራል የሚያዳምጥ የለም፡፡

ዓለማችንን የለወጡ ድንቅ አሳቢያን ከመንጋው ተነጥለው ነው የሚደንቁ ሃሳቦቹን የቀመሩት፡፡ መንጋው መንጋጋት ነው ስራው፤ በማጨብጭብና በመጠቆም ነው የሰለጠነው፤ በማውገዝና በመርገም ነው አንቱታ ያተረፈው፡፡ መንጋው ሲወድህ ከፍ አድርጎ ይሰቅልሃል፤ ሲጠላህም አያዝንልህም፤ ካስቀመጠህ አንስቶ ፈጥፍጦ ነው የሚጥልህ፡፡ መካከለኛ ነጥብ የለውም፡፡ ሚዛን፣ መጠን፣ ልክ አያውቅም፡፡ ማመጣጠን አይችልበትም፡፡ በአንድ ድክመትህ ሁሉንም ጥንካሬህን አሽቀንጥሮ ይጥላል፡፡ ለይቶ መውቀስን አልለመደም፡፡

ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ‹‹አዕምሮ የሌለው ሕዝብ ስርዓት የለውም›› ያሉት ይሄ ዘመን ቀድሞ ታውቋቸው ቢሆን ነው፡፡ እውነታቸውን ነው አዕምሮ ከሌለ ስነምግባር የለም፡፡ ሞራል፣ ስርዓትና ህግ የሚያከብር ዜጋ የሚኖረው በጎ አዕምሮ ሲኖር ነው፡፡ ዛሬ ሐገራችን ስርዓት አልባ ሆናለች፡፡ ነጋዴው ስርዓት የለውም፣ መምህሩም ሆነ ተማሪው በስርዓት አይመራም፤ ሐኪሙ መሃላውን ረስቶ ለጉንፋን በሽታ ላብራቶሪ የሚያዝ ነጋዴ ሆኗል፡፡ ሃይማኖተኛው፤ ሰበባኪው ስብዕና ከመገንባት ይልቅ የራሱን ገፅታ ነው እየገነባ ያለው፡፡ ሃይማኖቱን የሚከተል ሳይሆን ሰባኪን የሚከተል ምዕመን ነው እየተመረተ ያለው፡፡ ፈሪዓ እግዚአብሔር፣ በህግ አምላክ፣ ይሉኝታና እፍረት ተሸርሽሮ አልቋል፡፡ ዳኛው ጉቦኛ፤ ህጉ ፍትህ አልባ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ባልና ሚስት ጎጆአቸውን ለትርፍ የተቋቋመ ተቋም አስመስለውታል፤ ፍቅር የቤታቸው ዋልታ መሆኑ ቀርቶ በንግድ ህግ የሚመራ ሆኗል፡፡ መንግስትም የስርዓት ምንጭ መሆን ሲገባው ጭራሽ የሀገር ስርዓትን የሚያወድሙ የትላልቅ ህጋዊ ሌቦች መፈልፈያ ምንጭ ሆኗል፡፡ ባለስልጣኑም የቀረችዋን አንጥፍጣፊ ስርዓት ከማስቀጠል ይልቅ አጥፊ ስርዓት እየተከለ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ.... አዝማሪው፡-

‹‹ወግጂልኝ ዜማ ወግጂልኝ ቅኔ፣
ወንዶች በዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡››

እንዳለው በጉልበትህ ሳይሆን በአስተሳሰብህ ወንድ ሁን፡፡ የጎጥ ፖለቲካን፣ ጠባብ አስተሳሰብን ወግድልኝ በለው፡፡ ወንድ ሁን ማለት በሃሳብህ ጠንክር ለማለት ነው፡፡ ወንድ ሁን ማለት በተለየ ሃሳብ ከፍ ብለህ ብረር ማለት ነው፡፡ እንደፔንዱለም የወረት ንፋስ በሚወዘውዘው መንጋ አትሸነፍ፡፡ በአስተሳሰብህ፣ በአተያይህ፣ በምግባርህ፣ በስራህ የተሻለ ሰው ሁን! ከሁሉ ከሁሉ በአስተሳሰብህ ደፋር ሁን! ሰው ሃሳብን ሲደፍር ሰውነቱ ይበለፅጋል፤ ሕሊናው ይጎለምሳል፤ ንግግሩ የጣፈጠ ይሆናል፡፡ ራስህን አድምጥ፣ ተፈጥሮን አድምጥ፣ ዘመኑን አድምጥ፣ ሌሎችን አድምጥ! ቅዱሱ ቃል እንደሚለው ‹‹ለመስማት የፈጠንክ፤ ለመናገር የዘገየህ ሁን!››፡፡ የእንጀራ ዕውቀት ብቻውን የትም አያደርስህም፡፡ የልብ ጥበብም፣ የሕይወት ዕውቀትም ያስፈልግሃል፡፡ ሕሊናህን ከፍ አድርገህ ከፍ ከፍ በል፤ ልብህን አብስለህ እንደልብህ ኑር፡፡ ብዙ ሰው ባላሰበበት መንገድ ለማሰብ ድፈር! Dare to think the unthinkable!

ቸር ጊዜ!

_____________________
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
እሁድ ጥር ፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.

Like
Comment
Share
avatar

Meti Arega

Ya
Like
· Reply · 1673775807

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

avatar

Aser Berhanu

Greay
Like
· Reply · 1673778619

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

avatar

Ake Akuni

OK
Like
· Reply · 1673790674

Delete Comment

Are you sure that you want to delete this comment ?

Load more posts

Unfriend

Are you sure you want to unfriend?

Report this User

Edit Offer

Add tier








Select an image
Delete your tier
Are you sure you want to delete this tier?

Reviews

Pay By Wallet

Add New Address

Delete your address

Are you sure you want to delete this address?

Payment Alert

You are about to purchase the items, do you want to proceed?

Request a Refund