[ Photo ]
አሁን ደስተኛ ሆነህ እየኖርክ ነው?
የሰው ልጅ ሞትን የሚፈራው መኖር ስላልጀመረ ነው፤ አሁን እየኖርክ ነው? በሕይወት ነው ያለኸው? እስቲ እራስህን ፈትሽ! በሕይወት አለህ የሚባለው ዛሬን አመስጋኝና ደስተኛ ሆነህ መኖር ስትጀምር ነው። ማንም ሰው ሞትን ሳይሆን አለመኖርን ነው የሚፈራው አሁን እየኖርክ ያለኸው ሕይወት የሚያስደስትህ ከሆነ መልካም፤ በአንፃሩ ግን ህይወትህ ደስታ ከሌለው፤ አመለካከትህንና እይታህን በመቀየር ደስተኛ ሁን የምታስባቸው ነገሮች ሕልምህም የሚሳኩት የውስጥ ሰላምና መረጋጋት ሲኖርህ ነው።
ዳዊት ድሪምስ
ውብ ቀን ተመኘን
ምንድነው በአዕምሮህ የሳልከው ፍርሀት
ምንድንነው ከልጅነትህ ጀምሮ በአዕምሮ የተሳለለህ ፍርሀት? ለምንድነው የምትፈራው? ውስጥህ ይከብደኛል፤ አልችልም፤ አይሳካም በሚሉ ሀሳቦች ስለተሞላ ነው ትልቁ አቅምህን ሸብሽቦ ሕልምን እንዳታሳካ የሚጎትትህ፤ አሁን በሕይወት ብትኖርም አንድ ቀን ግን መሞትህ አይቀርም፤ የምትፈልገውን አርአያነት ያለው ስራ ሠርተህ ስምህን በመልካም ተግባር አስጠርተህ ትሄዳለህ ወይስ በውሸት ስዕል ፍርሃት ተሸብሽበህ ሕልምህን ሳታሳካ ተራ ሞት ትሞታለህ? ምርጫው የአንተ ነው! ስለዚህ እራስህን መርምርና የፍርሀትን ጥግ ፍፃሜ አበጅለት።
ዳዊት ድሪምስ
መልካም ቀን ተመኘን
Emran Naser
Delete Comment
Are you sure that you want to delete this comment ?
Meti Arega
Delete Comment
Are you sure that you want to delete this comment ?