ኢትዮጵያውያን ወደ ዱባይ በመሄድ ከአፍሪካ ሁለተኛ መሆናቸው ተገለፀ!
ኢትዮጵያውያን ወደ ዱባይ በመሄድ ከአፍሪካ ሁለተኛ መሆናቸውን ባይ የቱሪዝም ዲፓርትመንት የሰብ-ሰሃራ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ስቴላ ፉባራ ተናገሩ።በአፍሪካ ከናይጄሪያ ቀጥሎ ወደ ዱባይ በመጓዝ ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የገለጹት ዳይሬክተሯ፤ “የሚያደርጉት ጉዞ ወደ ቢዝነስ ቢቀይሩት የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናሉ”ም ብለዋል።
ዱባይ ከየትኛውም ሀገር በበለጠ ለኢትዮጵያ ቅርብ ናት ያሉት ዳይሬክተሯ፤ “ኢትዮጵያውያን ያሏቸውን በርካታ መስህቦች ለዓለም ተደራሽ ቢያደረጉ ተጠቃሚ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።በርካታ የሀገር ውስጥና የዱባይ ኩባኒያዎች የተሳተፉበት የዱባይ ቱሪዝም መድረክ በትናትናው እለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በ300 ሚሊዮን ዶላር 500 የኔትወርክ ማዕከላትን መገንባቱን አስታወቀ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን አዲስ አበባን ጨምሮ በ11 ከተሞች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት ኩባንያው በአንድ ወር ውስጥ 200 ሺህ ደንበኞችን አፍርቷል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ በ300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ 500 የኔትወርክ ማዕከላትን፣ ሁለት የዳታ ማዕከላትን እንደገነባም ተናግረዋል፡፡
ሰበርዜና❗️
ጀግናው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር የትግራይ ክልል ከተማ የሆነችውን አዲግራትን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ተረጋግጧል!!
በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚመራው በሁለት አቅጣጫ ማለትም በራማ በኩል እና በአክሱም በኩል ወደ አዲግራት የተንቀሳቀሰው ጥምር ጦር አዲግራትን ተቆጣጥሯል። ጀግናው የመከላክያ ሰራዊት እና ጥምር ጦሩ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ የህወሓትን ጀሌ በመጠራረግ እስካሁን
👉አዲግራት ከተማን
👉ሽሬ ከተማን
👉አክሱም ከተማን፣
👉አድዋ፣ ማይጸብሪ፣
👉የሃሙሲት፣ የበላጎ፣
👉አላማጣ፣ ኮረም እና
ሌሎች በርካታ አካባቢዎችን ነጻ አውጥቷል።
መቀሌም በመከላከያ ሀይላችን ከበባ ውስጥ ገብታለች!
ድል ለመከላክያ ሰራዊታችንና ጥምር ጦር🇪🇹
ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች የተባለችው የቤት ሰራተኛ በከባድ ግድያ ወንጀል ተደራራቢ ክስ ተመሰረተባት።
ተከሳሿ ወደ ማረሚያ ቤት እንድትወርድ በፍርድ ቤት ታዟል።
ተከሳሿ ህይወት መኮንን ሀይሉ በትናንትናው ዕለት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርባ ለምርመራ ማጠናቀቂ ለፖሊስ የ10 ቀን ቀጠሮ የተሰጠ መሆኑ ይታወሳል።
ሆኖም ከሳሽ ዓቃቢህግ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ከባድ የግድያና ውንብድና ወንጀል ችሎት በከባድ ግድያ እና ማስረጃ በማጥፋት ተደረራራቢ የወንጀል ክስ አቅርቦባታል።
ተከሳሿ ክሱ ከደረሳት በኋላ ጠበቃ የማቆም አቅም እንደሌላት መግለጿን ተከትሎ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላት ታዟል።
የቀረበባትን ተደራራቢ ክስ ለመስማት ለጥቅምት 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።
ተከሳሿ በችሎት ውስጥ ስታለቅስ ተስተውሏል።
ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረግ በግድያ ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር ውላ ከአንድ ወር በላይ ምርመራ እየተደረገባት እንደምትገኝ ይታወቃል።