2 yrs ·Translate

ወዳጄ!!

“እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ከወደደን መጥላት ፣ ከታመነልን መክዳት የለበትም ፡፡ እግዚአብሔርን ማግኘት በዘላለሞ እቅፍ ውስጥ መግባት ነው።ማደሪያ ቤቴ ፣ መተዳደሪያ ቀለቤ አንተ ነህ ። ያለፈውን በረከት አድፋፍቼ ዛሬም ስለምንህ ሃሳብ እንተሳሰብ ሳትል ትሰጠኛለህ የማትቀየም አንተ ብቻ ነህና። አምላከ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ አንተ የይለፍ ቃሌ ፣ የደኀንነት ነጭ ዓርማዬ ፣ የስኬት ምንጬ ነህ ። ያላንተ ማንተም በሰማይ መንግሥት እውቅና የለኝም ። መንፈሰ ጽድቅ ሆይ ፣ እኔን እኔው ሳውከው የመዳን ቀንድ ሁነኝ ። እኔን ሰው ሲያውከኝ ጋሻህ ይዘርጋልኝ ። እኔን ኑሮ ሲያውከኝ በረከትህ አለሁ ይበለኝ ። እኔን ቀኑ ሲያውከኝ መጽናናትህ ይድረሰኝ ። ጠዋት ለማታ ዓለም እያለፈ ነውና የጸናኸው አንተ ቡሩክ መንፈስ ሆይ አጽናኝ ። አሜን
ዲን አክሊል ዘሰዋስው
👇👇👇👇
@zsewasw
@zsewasw
@zsewasw

image