ባሻዬ! ከዚህ በፊት ያልኩትን ልደግመው ነው። ሰሞኑን ኪሎዬን ተመዝኜ 4 ኪሎ ግራም ያህል በመቀነሴ ደስ ብሎኛል። ያው እንግዲህ ከ108 ወደ 104 ኪሎ ግራም ዝቅ ብያለሁ። ስለዚህ አራቱ ኪሎ የጆንያው ሲሆን መቶው ደሞ የእህሉ ነው።
ከታች እንደምትመለከተው ቀበቶዬን ልሰረው ብዬ ብሞክር ምስኪኗ ጥንቸል በነብሩ ትበላለች። ዝም ብዬ ብተወው ደሞ በመካከል ያለው እባብ አደጋ ላይ ይወድቅብኛል። ኧረ ምን ይሻለኛል?
ባሻዬ! ቀበቶህን ቀይረው ብለህ እንደማትመክረኝ እገምታለሁ። ምክንያቱም ቀበቶ ማለት አገር ማለት ነው። አገር ደግሞ አይቀየርም።
#በሀገር_ምርት_ኩራ
mulu ketema
Delete Comment
Are you sure that you want to delete this comment ?