{እየቅል መልስ ያለው እየቅል ሰውነት}
በሰውኛ እውቀት ከሰው የላቀን ሰው
በራሴ ምልከታ አድንቄ ልሸልም፥
ሃሎ መባባያ ካርድ አዘጋጅቼ
መልሱ ያረካኝን በመልስ ላስደምም፥
ዓለም "ዓለም" ኾና የተቀመጠችው
ምንድን ላይ ነው? ብዬ ጥያቄ ብጠይቅ፥
ሰው ሐሳብ አዋጣ ብዙ መልስ አገኘኹ
አንድ የሚያስፈግግ አንድ የሚያስደንቅ፥
ሔዋን እንዲህ አለች፥አዳም እንዲህ አለ
ብቻዬን አልቻልኹም ነይ አብረን እንሳቅ፥
{ዓለም ምንድን ላይ ናት?}
(የዓለም ሰዎች ላይ)
ለካ ላይኾንልን
ተሸክመናት ነው ውልግድግድ ያልነው?
(የሰው ህሊና ውስጥ)
እውነትም እውነትም
እሷን ስናስብ ነው እኛኑ የጣልነው?
(ህዋ ላይ፥ካርታ ላይ)
ባዶ ማንነት ላይ
ባዶ ዓለምን መሳል እንደምን ተቻለን?
(ኢየሱስ መዳፍ ላይ)
እሱ ራሱ ፈቅዶ
ይዞልን ነው ለካ መኖር የቀለለን?
(ደጋግ ሰዎች ላይ)
ክፋታችን መኻል
እነሱ ኖረው ነው ምሕረት የከበበን?
(የሰው ልጆች ስም ላይ)
መጠሪያ ኾናን ነው
ስም አልገልጸን ብሎ ግብራችን ስም ያጣ?
(አዕምሯችን ውስጥ)
እንዴት አድራ ይኾን?
ስናሰላስል ነው መልካችን የታጣ?
(ልባም ሴት ልብ ውስጥ)
እንደምን አምነናት
ዓለምን ላ'ንዲት ሴት አደራ ሰጠናት?
(የእግዚአብሔር ቃል ላይ)
ለካ በ'ሱ ቃል ነው
ዓለም ሰው የኾነች ሰው ዓለም የኾናት?
(ህጻናት ልብ ውስጥ)
የገነተረ ዓለም
ጮርቃ ልቦና ውስጥ እንደምን ይኖራል?
(ጥቁር ጨለማ ላይ)
ካልጠፋ ብርሃን
ሰው እንዴት ራሱን ጽልመት ላይ ይሰራል?
(ምንም አካላት ላይ)
ምንም ብሎ አካል
አልቦ ብሎ አለ እንደምን ይኾናል?
(መሬት ላይ፥ሰማይ ላይ)
የመሬት ላይ መሬት
የሰማይ ላይ ሰማይ ቆሙ ምን ያኽላል?
(ምህዋረ መሬት ላይ)
መጓዝ የቀለለን
በማናውቀው መንገድ እየተጓዘች ነው?
(የሰው ከንቱነት ላይ)
ጅላጅል የኾነ'ው
ከንቱነታችን ላይ እያናወዘች ነው?
(መቶ ብር ካርድ ላይ)
ክብር የቀለለን
አየር ተሸክማ እየነዳችን ነው?
(እናት ላይ፥ሚስት ላይ)
እናት ምን በወጣት?
ሚስት ምን በወጣት እዳዋ ይገዝፋል?
(የጎረምሳ ጭን ላይ)
ወጣት ምን በወጣው
እሳት ገላ ይዞ እሳት ይታቀፋል?
(ሳጥናኤል እጅ ላይ)
ይንን መጠርጠር ነው
የቆመን ከመጣል እሱ መች ይሰንፋል?
(የረጋ ውሃ ላይ)
በእፍኝ የጠማን
ዓለምን ሊሸከም ከወዴት ይጎርፋል?
(እኔ ምን አውቄ?)
ገም'ቶ ከመክሰር
አቅምን አውቆ ማደር ከማወቅ ይሰፋል፥
_
ሔዋን አፏን ከፍታ ብዙ ተናገረች
አዳም አፉን ከፍቶ እልፍ ቃል አወጣ፥
አንድ መልስ ሽቼ በአንድ ቃል የጻፍኹት
አንድ ጥያቄዬ ብዙ መልስ አመጣ።
ከኹሉም ከኹሉም እኔን የገረመኝ
"መቶ ብር ካርድ ላይ" ብሎ የመለሰው፥
ብዙ መንገድ ያላት ሰፊ ዓለም ታቅፎ
ሰው መሻቱ ላይ ነው የሚመላለሰው፥
(እንኪ የእኔን እውነት)
ባ'ንድ ስም ሰውነት አንድ ዓለም ላይ ቆሞ
ሰው እውቀቱ ሌላ ሰው እምነቱ እየቅል፥
አንቺ ምንም ላይ፥ዓለም አንቺ ላይ ናት
ሌላ መልስ የለኝም እኔ በ'ኔ በ'ኩል።
ወደ ስኬት ለመገስገስና ስኬታማ ለመሆን የሚከተሉት በትኩረትና በአንክሮ አስተውልና ተግባራዊ አድርግ፦
1. ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!
ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፣
ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።
➋. የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም!
ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።
➌. መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል!
ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ?
እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።
➍. ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!
►በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ!
►ለሰዎች ክፉ አትመኝ፣
►በሃዘናቸውም አብረህ እዘን፣
►ሰዎች ሲያዝኑ አትደሰት፣
►ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።
➎. በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!
ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።
➏. መክሊትህን ፈልግ!
►ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ?
►ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና።
አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት። አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው።
►ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ነው?
►ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው?
►የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው?
►ምንድነው ???
እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው፣
"ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ። በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።
➐. መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል!
ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀየር ብቃት አለው። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል።
-መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፣
-መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።
➑. "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አባባል አስታውስ!
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል። ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፣ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።
➒. ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!
ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።
➓. በማንም ላይ አትፍረድ!
►የመፍረድ ኃላፊነት በፍፁም የለህም።
►ፍርድ የፈጣሪ ነው።
►ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል፣
►ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት።
►የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል።
➊➊. መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ መሆኑን አትርሳ!
የጓደኛህን ስሜት ለመረዳት ሞክር፣ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት፣ አበረታታው፣ እንደማይጠቅም አትንገረው፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን።
➊➋. መልካም ጓደኛ ሁን!
መልካም ጓደኛ፦ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል፣ ታድለሃል። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ። ነገር ግን ያለምክንያት ከሄድክ በምክንያት አትምጣ። በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ ጉዳት እንጂ ጥቅም የሌላቸው ሰዎች በራሳቸው ሰዓት ከሕይወትህ ሲወጡ እጅግ መታደል ነው።
➊➌. ከአጓጉል ሀሳብና ጭንቀት ራስህን ጠብቅ!
ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትንና፣ ሀዘንን ያስከትላል። ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ፣ መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ፣ አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ። ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር።
➊➍. ደግነት አይለይህ!
ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው፣ "ያስከፍላል" ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ። እናም ዘወትር ደግ ሁን። ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸውና ሰላማቸው ልክ የለውም።
➊➎. ደስታህንና ሰላምህን ካንተ ዘንድ አኑራቸው!
ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ!
ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው።
►በራስህ በአፈጣጠርህ→ደስ ይበልህ፣
►ውለህ በመግባትህ→ደስ ይበልህ፣
►በአለህ ትንሽ ነገር→ደስ ይበልህ።
➊➏. ፍቅርን ፈልጋት!
♡ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ።
♡በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።
➊➐. ዘመንህን ከርኩሰት ጠብቀው!
እድሜህን በተመለከተ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳየኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።
➊➑. "መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም አይጎዳም" የሚለውን አባባል አስታውስ!
ይህም ማለት የሕይወት ዓላማ ሊኖርህ ይገባል ማለት ነው። የየኖሩበት እድሜ ትንሹም ቢሆን በቂ ነው ይባላል። የማቱሳላ እድሜው እንጅ የሰራው ስራ አይታወቅም፣ "ኖሮ ሞተ" ብቻ ከመባል ፈጣሪ አምላክ ይጠብቅህ፣
መኖርህ ሰዎችን ካልጠቀመ መሞትህ ላይጎዳቸው ይችላል፣ መኖር ማለት መጥቀም መጠቃቀም ነው። ለራስ መኖር፣ ለሌሎች መኖር።
➊➒. ከማማረር ማመስገንን ልመድ!
የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ረስተን፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው። ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል። በማማረር በረከት የለም።
#funny funnye fun staf
#ይህን_ከታች_የምታነቡትን_ምክር_ወይንም_ጥበብ_ቢጤ_ማንበብ_ብዙ_መፅሐፍትን_የማንበብ_ያህል_ነው።
📚 መልካም ንባብ📖
🔹🔸በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
🔹🔸ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
🔹🔸የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። ነገርግን እስከ አለህበት ጊዜ ሰለቆየህ ተመስገን በል።
🔹🔸ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።
🔹🔸የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
🔹🔸ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ። መልካምነት ለእራስ መሆኑኑንም አትዘንጋ።
🔹🔸ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
🔹🔸ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።
🔹🔸እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
🔹🔸ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
🔹🔸በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
🔹🔸የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
🔹🔸ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
🔹🔸መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
🔹🔸ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
🔹🔸ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
🔹🔸ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
🔹🔸ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
🔹🔸የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።
🔹🔸ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
🔹🔸ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
🔹🔸ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ሀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።
🔹🔸እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
🔹🔸 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ።